“Application of Expanded Polystyrene/EPS/ Geofoam in Civil Engineering Projects” በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በማዕከላዊ ጎንደር ፣በምዕራብ ጎንደርና በሰሜን ጎንደር ለሚገኙ የውኃ፣ የመንገድ ፣የኮንስትራክሽ፣የዲዛይን ባለሙያዎች፣አማካሪ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በተገኙበት “Application of Expanded Polystyrene /EPS/Geofoam in Civil Engineering Projects” በሚል ርዕስ ሰኔ 2 እና 3/2013 ዓ.ም በአጼ ፋሲል ግቢ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ዲን ተወካይና የአካዳሚክ ም/ዳይሬክተር ኢንጅነር ዮኃንስ ኃይለማሪያም የጅኦፎም አተገባበርን ወደ ሲቪል ፕሮጀክት ለማምጣትና ቴክኖሎጅውን ለማላመድ ታስቦ ይህ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
በክልለሉ መንግስትና የአማራ ህንጻ ስራዎች ድርጅት በትብብር የተጀመረው ይህ አዲስ የህንጻ ተገጣጣሚ ክፍሎች እና የድልድዮች አሰራር የቴክኖሎጅ ከዋጋ፣ ከጊዜ ከጥራትና ከጉልበት ወጭ ቁጠባ አንጻር አዋጭ መሆኑን የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የድህረ ምረቃ አስተባባሪ ዶ/ር ይበልጣል ዘሬ ተናግረዋል፡፡




