የሀገሪቱን አበይት ተግዳሮቶች ለተመራማሪዎች የሚጠቁም አውደጥናት ተካሄደ
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር “Grand Challenge Ethiopia Orentation Workshop for University Researchers”በሚል የሀገሪቱን አበይት የጤና ችግሮች በምርምርና በፈጠራ ለመቅረፍ የሚያስችል አውደጥናት ሰኔ 3/2013 ዓ.ም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ተካሄደ።

በአውደጥናቱ በጤና ሚኒስቴር ስር ከሚገኘው “Armauer Hansen Research Institute” የምርምር ማእከል እና”Grand Challenge Ethiopia” የመጡ እንግዶች፣ የዩኒቨርሲቲአችን ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን እና ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የጤና ችግሮችን በፈጠራ ስራዎች በመታገዝ የጤና ስርአቱን እንዴት እናሻሽላለን? በቀጣይ የምንጠብቀው የፈጠራ ስራ ምንድን ነው? የሚለውን በደንብ አውቆ ትላልቅ ግራንቶችን ለማሸነፍ ተመራማሪዎች በሚገባ መዘጋጀት እንደሚገባቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቢኒያም ጫቅሉ በአውደጥናቱ መክፈቻ ላይ አብራርተዋል፡፡




