በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚካሄደው የድህር ምረቃ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ እንደቀጠለ ነው፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የምህንድስና ዘርፎች ማለትም በኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ት/ት ክፍል (PhD in Electrical & Power Engineering) ፣ እና በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ት/ት ክፍል (PhD in Process Engineering, MSc in process Engineering, MSc in Eniviromental Engineering and also MSc in Industrial Pollution Control Engineering) የስርአተ-ትምህርት ግምገማ አውደ ጥናት ሰኔ 23/2013 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ አካሂዷል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሰቲ ሁኖ መለየቱን ተከትሎ በድህር ምረቃ ትምህርቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የዩኒቨርሰቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የምህንድሰና ድህረ ምረቃ ዘርፎች በ3ኛ ድግሪ- ብዛት 3 እንዲሁም በ2ኛ ዲግሪ- ብዛት 8፣ በአጠቃላይ 11 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን በሚቀጥለው የትምርህርት ዘመን ለመክፈት የስራዓተ ትምህርት ግምገማዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡




