የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመክፈት የውጭ ስርዓተ ትምህርት ግምገማ አውደ ጥናት /National External Curriculum Review Workshop/ ተካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ /Para-clinical studies/ ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት /PhD in veterinary parasitology and PhD in veterinary Microbiology/ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመክፈት የውጭ ገምጋሚዎችን ያሳተፈ የስርአተ ትምህርት ግምገማ ዝግጅት አውደ ጥናት /National External Curriculum Review Workshop/ የኮሌጁ አመራሮች፣ ምሁራንና የውጭ ገምጋሚዎች በተገኙበት ሰኔ 25/2013 ዓ.ም በኮሌጁ አዳራሽ ተካሄደ፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ በድህረ ምረቃ ትምህርቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ሰዓት 134 የድህረ ምረቃ እና 87 የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞችን እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በዶ/ር ሽመልስ ዳኛቸው እና የማይክሮባዩሎጅ ትምህርት ክፍል መምህር በዶ/ር አንዋር ኑሩ በአውደ ጥናቱ የቀረበው የሶስተኛ ዲግሪ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ጥናት ቀርቦና ሰፊ ውይይት ተደርጎበት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡




