በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ሊተገብሩ የሚገቧቸውን እና ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ግዛቸው ሙሉጌታ እንደገለጹት በዚህ ዓመት 3,664 ተማሪዎች መዝግበን ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት አድርገን የጠበቅን ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ለተማሪዎቻችን አጠቃላይ መረጃ የሚሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማሩ መሀመድ በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው በማራኪ፣በአጼ ቴዎድሮስና በፋሲል ግቢዎች ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ አሰልጣኞች አማካኝነት ተማሪዎች ሊተገብሯቸው የሚገባቸውንና የተከለከሉ ተግባራት የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል ፡፡





