ጸሐፊ-ተውኔት ደራሲና አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጆ ልምዷን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካፈለች!!
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ የቲያትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ታዋቂዋን አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጆን በመጋበዝ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ የሚታሰብበት የኪነ-ጥበብ ጉባዔ በማራኪ ግቢ ታህሳስ 15/2013 ዓ.ም. አካሂዷል፡፡
የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አገኘሁ ተስፋ አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጆ ያላት ከፍተኛ የሆነ የህይወት ተሞክሮ በርካታ በመሆኑ ከዚሁ ልምዷ ብዙ ነገሮችን መውሰድ እንደሚቻል በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው ተናግረዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ በበኩላቸው አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጆ የዩኒቨርሲቲያችን ጥሪ አክብራ በመምጣቷ በዩኒቨርሲቲው ስም አመስግነዋል፡፡ አርቲስት አለምፀሃይ ለሀገራችን የኪነ-ጥበብ እድገት እጅግ ከፍተኛ አሰተዋፅኦ ያበረከተች በመሆንዋክብር ይገባታል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ኪነ-ጥበብ ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝ የሆነ ዘርፍ በመሆኑ በዚህ ሙያ ውስጥ ያዳበረችውን እውቀት ለዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ልታካፍለን በመምጣቷበ ድጋሚ አመስግነዋል፡፡
አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጆ “ጎንደርን አውቃታለሁ የታሪክና የባህል ሀገር ናት ህዝቡም እንግዳ ተቀባይና አሰተዋይ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ወጣቶች በእውቀትና በችሎታቸው እያደጉ በማዬቴ ተደስቻለሁ፡፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲም ለኪነጥበብ እድገቱ የሚጠቅሙ ተግባራትን በቲያትር ጥበባት ትምህርት ክፍል እየሰራ መሆኑን ለመገንዘብ ችያለሁ” በማለት ተናግራለች፡፡
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
***********************************
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም







