የመልካም አስተዳደርና የት/ልማት ሰራዊት ግንባታ ዕቅድ ተገመገመ
የዩኒቨርሲቲያችን የካዉንስል አባላት በመልካም አስተዳደር እና በትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ የ2008 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማ በዩኒቨርሲቲዉ የእንግዳ ማረፊያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡
ጥቅምት 25/2008 ዓ.ም የተካሄደውን የዕቅድ ግምገማ በንግግር የከፈቱት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ተወካይ ሲሆኑ፤ባደረጉት ንግግር የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጣችን ለዕቅዳችን መሳካት ከፍተኛ ዋጋ ያለዉ በመሆኑ ዘንድሮ 3ኛ የወጣዉ ዩኒቨርሲቲያችን ያሉብንን ክፍተቶች ከሞላን አንደኛ መዉጣት የማንችልበት ምክንያት የለም፡፡ ይህን ተግባር ለመፈፀም ደግሞ የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ወሳኝ ድርሻ አለዉና በተደራጀ መልኩ ለመስራት ይህን ዕቅድ አዘጋጅተናል ፤ በመሆኑም የዩኒቨርሲቲያችን የካዉንስል አባላት ዕቅዱ ላይ የጠለቀ ውይይት በማድረግ ማዳበር እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡

የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንት ተወካይ ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ ለካውንስል አባላቱ ንግግር ሲያደርጉ
የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ዕቅድ እና የትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታ ዕቅድን አቶ ፈንታሁን ጫኔ የተቋማዊ ለዉጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዕቅዱን በመተንተን አቅርበዋል፡፡

አቶ ፈንታሁን ጫኔ የተቋማዊ ለዉጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዕቅዱን ሲያቀርቡ
ከካዉንስል አባላት የተለያዩ ሃሳቦች ቀርበዉ ዕቅዱ የዳበረ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የልማት ማነቆ ነዉና ከፍተኛ ትኩረት ልናደርግ ይገባል በማለት የካውንስል አባላቱ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡የትምህርት ልማት ሰራዊት በዩኒቨርሲቲዉ ያሉ ተግባራትን በተደራጀ መልኩ ለመፈፀምና ልናሳካ የምንፈልገዉን ግብ ለመምታት የሚያስችል ታላቅ አደረጃጀት በመሆኑ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የሚሉ ሃሳቦች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በዉይይቱ የዩኒቨርሲቲዉ ካዉንስል አባላት ለመልካም አስተዳደር መስፈን በአንድ አቋም መረባረብ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
//ሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት//

