የፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማ ወርክሾፕ ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት የሚደገፍ የማህበረሰብ አገልገሎት በ14 የሜጋ ፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ የግምገማ ወረክ ሾፕ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጋቢት 30/2008 ዓ.ም በሳይንስ አንምባ አደራሽ አካሄደ፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ
ስብሰባዉን በመክፈቻ ንግግር የስጀመሩት የጎንድር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ አንዳሉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስተምሮ ከማስመረቅ ባሻገር ትልቅ ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገባዉ ችግር ፈች ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነዉ ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት የተለያዩ እቅዶች ሲዘጋጁ የማህበረሰቡ ፍላጎት መሰረት የደረገና በማህበረሰቡ ፍላጎት የተቃኙ ሊሆኑ እንደሚገባዉ አፅንኦት ሰጠዉ ተናግረዋል፡፡
የቀረቡት ሜጋ ፕሮጀክቶች በጥናትና ምርምር፣ በጤና፣ በገብርና እና በአቀም ገንባታ በአጭርና በረዥም ስልጠና ላይ ሲተገበሩ የነበሩና በመተግበር ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በሃላፊዎች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በማንሳት ጠንካራዉን የበለጠ ተጠናክሮ እና አድጎ ወደ ሌሎች ማህበረሰብ መድረስ እንዳለበትና መሻሻል የሚገባዉን ለይቶ ከሌሎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ማሻሻል እንደሚገባ ተገልጧል፡፡
ፕሮጀክቶች ሲተገበሩ የተለየዩ ችግሮችን ቢያጋጥሙም የትራንስፖርት ችግር ከሁሉም የበለጠ እንደነበረ በተለይ የፊስቱላ ህክምናን በአግባቡ ለመስጠት እንቀፋት አንደሆነባቸዉ የፕሮጀከቱ አስተባባሪ አቶ አዝመራዉ አድጎ ገለጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለኮሶየ ፕሮጀክት የዉሃ እጥረት ትልቁ ፈተና እንደሆነ የፕጀክቱ ሃላፊ ፕሮፌሰር አምሳሉ ፈለቀ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዉጭ አጋዥ ድርጅቶች ቃል የገቡትን ገንዘብ በወቅቱን መልቀቅ አለመቻላቸዉ ተጨማሪ እነቅፋት እነደሆነባቸዉ የፕሮጀክት አቅራቢዎች ገልጸዋል፡፡
የትራንስፖርት ችግርን በተመለከተ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አብረሃ በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ አመላክተዋል፡፡ በመጨረሻም ዉይይቱ ለፕሮጀክቱ ሃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም ለአጋር አካላት የእዉቅና የምስክር ወረቀት ሰጠዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ይላቅ አለባቸዉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ሪፖርተር
አርታኢ፡ ደምሴ ደስታ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

