ስለእናት ንብ አረባብ ስልጠና ተሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምና ፋካሊቲ ለጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከ5 ቀበሌ ለተወጣጡ 45 አርሶ አደሮችና 12 ሙያተኞች ስለ እናት ንብ አረባብ ዘዴ ግንቦት 20/2008 ዓ.ም በማክሰኝት ከተማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳራሽ ሽልጠና ተሰጠ፡፡

እረዳት ፕሮፌሰ አቶ ማለደ ብሃኑ የህክምና ፋካሊቲ መምህርና የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ
የእናት ንብን ሰዉ ሰራሽ በሆነ የማባዛት ዘዴ በመጠቀም አንድ ቀፎ ንብን ወደ ብዙ ቀፎ ንቦች በማባዛት ለአርሷደሮች፣ ለስራ አጥ ወጣቶችና ለሴቶች ተጨማሪ ገቢ በማሰገኘት ድህነትን መቀነስ እንዲሁም የአካባቢን ስነ-ምህዳር ለማሻሻል ቁልፍ ዘዴ አንደሆነ የህክምና ፋካሊቲ መምህርና የማህበረሰብ አግልግሎት አስተባባሪ እረዳት ፕሮፌሰር አቶ ማለደ ብርሃን ተናግረዋል፡፡

አቶ ሀይሉ ብርሃኑ የሰ/ጎንደር ዞን የእንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ተጠሪ ስልጠና ሲሰጡ
ስለጠናዉን በጽንስ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ሲሆን ስልጠናዉን የሰጡት የሰሜን ጎንደር ዞን የእንሰሳት ሀብት ልማት ማሰፋፊያ ተጠሪ የጽ/ቤት ባለሙያ አቶ ሀይሉ ብርሐኑ የስልጠናዉን አላማ አስመልክቶ እንዳሉት ስልጠናዉ ሶስት ዋና ዋና ተገባራት አሉት እነዚህም የሽግግር ቀፎ ከነ ክዳኑ በተግባር መስራት፣የጉንዳንና የቅምጫጭሪት ወይም ቁንጫጭ መከላከያን ከዘመናዊና ከሽግግር ቀፎ ማስቀመጫ ጋር መስራት እና ቀላል የሚባሉ ህብረ ንብ የማባዣ ዘዴን ጽንስ ሃሳቡን መገንዘብና በተግባር መስራት እንደሆነ ገላጸዋል፡፡ አቶ ሀይሉ ብርሐኑ አያይዘዉም አብዛኛዉ የስልጠናዉ ከፍል የተግባር ስልጠና ስለሆነ ሁሉም ሰልጣኞች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸዉና ሙያተኞች ለተግባራዊነቱ ትልቅ ሃላፊነት እንደሚጣልባቸዉ ተናግረዉ ስልጠናዉ ተጀመረ፡፡ ስልጠናዉ በሰልጣኞች የነቃ ተሳትፎ አና ባሰልጣኙ ጥንካሬና ያሰልጣኝነት ብቃት ታጅቦ ስለጠናዉ ዉጤታማ በሆነ መልኩ ተሰጥቷል፡፡

ሰልጣኞች በተግባር የሽግግር ቀፎ ሲሰሩ
ከስልጠናዉ በኃላ አንዳንድ ሰልጣኞችን አነጋግረናል፡፡ ሰልጣኞች እንደነገሩን ንግስት ንብን በነሱ አገላለጽ አዉራ ንብን እንዴት ዘመናዊ በሆነ መንገድ ማባዛት እንደሚቻል እነደማያዉቁና በምትኩ ባህላዊ ቀፎን ዛፍ ላይ በመስቀል አልፎ ሄያጅ ንብን ካዘጋጁት ቀፎ ለማስገባት ወራትንና አላፍ ሲልም አመታትን ሲጠባበቁ እንደኖሩ ገልጸዋል፡፡ አሁን ግን አሉ ሰልጣኞች አሁን ግን ምስጋና ለጎንድር ዩኒቨርሲቲ ይግባዉና ባገኘነዉ የጽንስ ሀሳብና የተግባር ስላጠና መሰረት ንቦችን እንዴት ከጉንዳንና ከቁንጫጭሪት መከላክል አንደሚቻል፣ የሸግግር ቀፎን ከሁለት አይነት ማሰቀመጫ ጋር እንዴት መስራት እንደሚቻል አና እናት ንብን በቀላል ዘዴ ማራባት እንደሚቻል አዉቀናል፤ ስርተናልም፤ ወደ የቀበሊያችን ሂደንም ተግባራዊ እናደርገዋለን ለሌሎችም ተሞከሯችን እናሳያለን እንዲስፋፋም እናደርጋለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የእንሰሳት ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መልኬ በላይ እንደተናገሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለወረዳዉ እድገት በተለዩ ዘረፎች ስልጣና እና መሰል እጅግ አስፈላጊ የማህበረሰብ ስራዎችን አየሰራልን ይገኛል ምስጋናችን አጅግ የለቀ ነዉ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
እንደተባለዉ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለየዩ ቦታዎች ማለትም በጎንደር ከተማ፣ በተለያዩ ወረዳዎች፣ በአማራ ክልል በሚገኙ ዞኖችና አለፍ ሲልም በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠቸዉ መጠነ ሰፊ ስልጠናዎችና የተላያዩ የማህበረሰብ አገልገሎቶች ከመማር ማስተማሩና ከምርምር ስራዎች ባሻገር ለወገን ደራሽነቱን ለልማት እና ለሀገር እድገት ወሳኝ ተቋም መሆኑን በተግባር እያሳየ ነዉ፡፡
ዘጋቢ፡ ይላቅ አለባቸዉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ሪፖርተር
አርታኢ፡ ደምሴ ደስታ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

