የነባርና አዲስ ተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ማስተካከያ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎችን የሚቀበልበትን ጊዜ ቀደም ሲል በድረ-ገፅ ማሳወቁ ይታወቃል ሆኖም የቅበላ ጊዜውን በማስተካከል
-ነባር የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች የምንቀበለው ከመስከረም 27-29/2009 ዓ.ም ሲሆን፤
-አዲስ ተማሪዎችን ደግሞ ከጥቅምት 4-6/2009 ዓ.ም ድረስ ይቀበላል፡፡
ይህ ማስተካከያ በዩኒቨርሲቲው ፌስቡክ ገጽ የተለቀቀ ሲሆን፤ በተጨማሪም በቴሌቪዥንና በሬዲዮ የሚነገር ይሆናል፡፡
ለአዲስ ተማሪዎች ቀደም ሲል በሬጅስትራር የተሰጠው ማሳሰቢያ ማለትም፡-
– ከ9-12 ትራንስክሪፕት
– የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
-እንዲሁም የፓስፖርት መጠን ያለው በቅርብ ጊዜ የተነሳችሁት 8 ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመያዝ በግንባር እየቀረባችሁ እንድትመዘገቡ የሚለውና- ማንኛውም ተማሪ አንሶላ ብርድ ልብስና የስፖርት ትጥቅ ሊኖረው ይገባል፡፡- ከተጠቀሰው ጊዜ በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውንም ተማሪ የማናስተናግድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

