የ2009 ዓ.ም የነባርና አዲስ ተማሪዎች ቅበላ ጥሪ ማስታወቂያ
የጎንደር ኒቨርሲቲ የ2009 ዓ.ም አዲስና ነባር ተማሪዎችን የሚቀበልበትን ጊዜ ማራዘሙን ቀደም ብለን ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡ አሁን ግን ቅበላ ጊዜው የተወስነ ስለሆነ
– ነባር ተማሪዎች ከጥቅምት 10 – ጥቅምት 13/2009 ዓ.ም፤
– አዲስ ተማሪዎች ከጥቅምት 17/2009 – ጥቅምት 20/2009 ዓ.ም ድረስ መሆኑን እየገለፅን፤
ይህን መረጃ በዩኒቨርሲቲው የፊስቡክ ገፅ መመልከት የምትችሉና በተከታታይ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የ2009 ዓ.ም ሠላማዊና የስኬት ጊዜ እንዲሆንላችሁ ለነባርና አዲስ ተመዳቢ ተማሪዎቻችን እንመኛለን፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

