የኢኮኖሚክስ ት/ት ቤት ስልጠና ሰጠ፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ስር የሚገኘው የኢኮኖሚክስ ት/ት ቤት #impact evaluation methodology$ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለዘርፉ ለ2ኛ እና ለ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችና መምህራን ከጥር 7- 12/2010 ዓ.ም በት/ት ቤቱ የጥናትና ምርምር ማዕከል ስልጠና ሰጥቷል፡፡
[widgetkit id=8129]
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔ እንደተናገሩት፣ ከ80% በላይ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲው መምህራን በጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙ አውስተው ምሁራኑ ያላቸውን ሳይንሳዊ እውቀት ይበልጥ ለማሳደግ መሰል ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ስልጠናዎች የጎላ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡ ፕ/ር መርሻ ጫኔ ስልጠናውን የሚሰጡት ግለሰብ ዶ/ር ግርማ ተስፋሁን ፣በሀገር ውስጥና በተለያዩ የውጭ ሀገራት በመዘዋወር ያገኙትን ሰፊ እውቀት እና ልምድ ለወጣት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ለማካፈል ፈቃደኛ ሆነው በመገኘታቸው ያላቸውን ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከአነጋገርናቸው ሰልጣኞች መካከል የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ እና ከሰልጣኞች አንዱ የነበሩት አቶ ወርቅነህ አስማረ እንደተናገሩት በስልጠናው አዲስና ሳይንሳዊ ይዘትን ያካተተ የጥናትና ምርምር ዘዴ/#impact evaluation methodology$ በበቂ ሁኔታ መሰልጠን መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በስልጠናው ከዚህ በፊት የነበሩትን የእውቀት ክፍተቶች መሙላት የሚያስችል ሙያዊ እውቀትና ግንዛቤ ማግኘት እንደቻሉ የት/ት ክፍል ኃላፊው ገልጸውልናል፡፡
ዘጋቢ፡ አምሳሉ ግዛቸው
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

