በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ የምክክር መድረክ ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ ከአጋር አካላት ጋር ግንቦት 06/2008 ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
በውይይቱ ላይ ከክልል፣ ከሰሜን ጎንደር ዞን አና ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የመጡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች አንዲሁም የጎንደር ዩኒቨረሲቲ ፕሬዚዳንት፣ም/ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖችና፣ የማህበራዊ ሳይንስ መምህራን፣ እና የትምህት ከፍል ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታከለ ታደሰ በምክክር መድረኩ ለተገኙ ተወያዮች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ምስጋና አቅርበዉ ለልማትና እድገት ማነቆ የሆነዉን የመልካም አስተዳደር ችገሮችን ለመፍታትና የአስተዳደር ስርአቱን ከሙስናና ከአድሎ የፀዳ ለማድርግ ከፍተኛ ተኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ የከፍተኛ ተቋማት በአኮኖሚና ልማት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ሚና አንዳላቸዉ ገልጸዉ በሰው ኃይል ልማት፣ በቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ የሚሰሩ ምርምሮች ችግር ፈችና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆን እንዳለባቸዉና ዉጤት በሚያመጣ መልኩ ከአጋር አካላት ጋር በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንዳሉት ከ62 ዓመታት በፊት ዩኒቨርሲቲው ሲመሰረት በደንቢያ የወባ ወረርሽኝ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖችን መግደሉ የመለስተኛ ጤና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋም እንዲቋቋም መነሻ የሆነው፡፡ ይህ የሚሳየዉ የዩኒቨርሲቲው አመሰራረት የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ሲባል ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ ዩኒቨርሲቲዉ ብቁ ዜጎችን ማፍራት፣ ችገር ፈች ምርምሮችን ማካሄድ እና የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን መስራት እንደሆነ ተናግረዉ የየጎንደር ዩኒቨርሲቲ ብዙ ስራዎችን ቢሰራም ከክልል፣ ከዞንና ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በቅንጅት ባለመስራታችን የማህበረሰቡን ኢኮኖሚዉን አና ኑሮዉን ማሻሻል እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ይህን የዉይይት መድረክ ያዘጋጀዉ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወገናዊነቱንና ያሳየበት መደረክ ነዉ ካሉ በኋላ የተለያዩ ጥያቂዎችንም ጠይቀዋል፡፡ ከጠየቋቸዉ ጥያቄዎች መካከልም፡- በተለያዩ መስሪያ ቤቶችና ቢሮዎች ያለዉን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ለማሻሻል ዩኒቨርሲቲዉ ምን መስራት አስቧል? ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ያለዉ የትምህት ጥራት ተጓሏል፤ ስለዚህ ዪኒቨርሲቲዉ ይህን ችገር ለመቅረፍ ምን በማድረግ ላይ ነዉ? የተለያዩ የማሳ ቦታዎች ወደ ጫት እርሻነት እየተቀየሩና ከወጣት አስከ አዛዉንት ድረስ በዚህ አደገኛ ቅጠል ሱስ አየተለከፉ ናቸዉ ይህን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲዉ ያደረገዉ ጥናት አለ ወይ? ዩኒቨርሲቲዉ ከማህበረሰቡ ጋር እያደረገዉ ያለዉን ዉይይት አና የማህበረሰብ አገልግሎት ቀጣይነት ባለዉ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ ምን ታቅዷል? የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ከላይ ለተነሱት ጥያቄዎችና ዩኒቨርሲቲዉ እየሰራቸዉ ባሉት ስራዎች ላይ ተሰብሳቢ መምህራን፣ የትምህርት ከፍል ሀላፊዎች፣ ዲኖች፣ ምከትል ፕሬዚዳንቶች አንዲሁም ከክልል የመጡ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሁሉን የማህበረሰብ ችገሮች ዩኒቨርሲቲዉ ይፈታልን፣ የገንዘብ አርዳታ ያድርግልን ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ዩኒቨርሲቲዉ ችገሮች ላይ ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ፣ የተላያዩ የአቀም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የቴክኖጅ ሸግግር በማካሄድ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ሰራዎችን አንዲሰራ ማድረግ አንደሚገባ አጽንዖት ሰጠዉ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ የጣናን ሀየቅ ህልዉናን እየተፈታተነዉ የለዉን የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ የተላያዩ ጥናትና ምርምሮች እየተካሄዱ እንዳሉና ዉጤቱም ደስ የሚያሰኝ እነድሆነ ተገልጧል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ አረሙን ማረሚያ ማሽን በመስራት ላይ አንደሚገኝና ስራዉ 50 ፐርሰንት አንደደረሰ ተገልጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከገብስ ዉጭ ዳጉሳ ቢራ የሚሆነበት መንገድ ላይ፣ ባህላዊ ቀለም ማዘጋጀት ላይ፣ ባህላዊ ህክምና ላይ፣ በጫት ላይ፣ በኖራ ድንጋይ ላይ፣ ባዮጋዝ እና ባዮ ፊዉል ላይ ዩኒቨርሲቲዉ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ እና ባብዛኞቹ ላይም አመሪቂ የሆነ ዉጤት እየተገኘ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ዘጋቢ፡ ይላቅ አለባቸዉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ሪፖርተር
አርታኢ፡ ደምሴ ደስታ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

