150ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕት ዳግማዊ አፄ ቴወድሮስ በዓልን ለማክበር ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 150ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕት ዳግማዊ አፄ ቴወድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ በዓልን አማራ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል፡፡
[widgetkit id=8818]
ከነዚህ ዝግጅቶች መካከል ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ ባለሙያዎች፣ ከወረዳ ዞንና ክልል ባህልና ቱሪዝም የሚመለከታቸው አካላት፣ የጎንደር ኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህራን እና ሌሎች አካላት የተሳተፉበት አፄ ቴዎድሮስ የተወለዱበትን፣ ያደጉበትን፣ ሀይማኖታዊ ትምህርት የተማሩበትን፣ የነገሱበትን፣ የኢንዱስትሪ አብዮት ያካሄዱበትን፣ በመጨረሻም ህይወታቸው ያለፈበትን በአጠቃላት የአፄው አሻራ ያረፈፉባቸውን ስፍራዎች የመጎብኘት ዝግጅት አንዱ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አስሩም ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉበትና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው የቁንጅና ውድድር ሌላው ዝግጅት ነው፡፡
የ150ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕት ዳግማዊ አፄ ቴወድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ በዓል አካል የሆነው የጥያቄና መልስ ውድድር መጋቢት 26/2010 ዓ.ም ማራኪ ግቢ በሚገኘው አልሙኒየም ህንፃ ተካሂዷል፡፡ ከሁሉም ግቢ የተውጣጡ 56 ያክል ተማሪዎች በቡድንና በተናጠል ለውድድር ቀርበዋል፡፡ የመወዳደሪያ ጥያቄዎቹ በኢትዮጵያ ታሪክና በአፄ ቴዎድሮስ ስራዎች ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ፣ ውድድሩ በ3ዙር ተካሂዷ፡፡ በመጀመሪያው ዙር 15 ተወዳዳሪዎች፣ በሁለተኛው ዙር 7 ተወዳዳሪዎች እንዲሁም በ3ተኛው ዙር 5 ተማሪዎች ለፍፃሜ ቀርበዋል፡፡ ተማሪ ዮሴፍ ንጉሴ እና ፍፁም አስማማው ከህግ ትምህርት ክፍል አንደኛ ሲሆኑ ተማሪ ቢኒያም ጎይቶም ከጆርናሊዝም ትምህርት ክፍል ሁለተኛ እንዲሁም ተማሪ እንዳየሁ ካሳና ባበይ ዘለቀ ከቱሪዝም ማኔጅመንት ትምህረት ክፍል 3ተኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩ ተጠናቅቋል፡፡



