የጎንደር ዩኒቭርሲቲና ጎንደር መምህራን ትምህርትኮሌጅ በጋራ ለመስራት ስምምነት አካሄዱ
የጎንደር መምህራን ኮሌጅ ከተመሰረተ 36 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ኮሌጁ ለዓመታት በርካታ ሙሁራንን በማፍራት የሚታወቅ ነው፡፡ ይሁን እንጅ በአሁኑ ሰዓት በትምህርት ጥራት፣ በሰው ሀብት ለማትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ችግሮች ተደቅነውበታል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ የጎንደር ዩኒቭርሲቲና ጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በጋራ ለመስራት ስምምነት አድርገዋል፡፡ በስምምነቱ የጎንደር ዩኒቭርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይንና የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን አቶ ስንታየሁ ነጋሽ የፊርማ ስነ-ስራቱን አካሂደዋል፡፡
[widgetkit id=8862]
የስምምነቱ ዋና ዓላማ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግና በቴክኖሎጅ የታገዘ የሰው ኃይል ለማፍራት እንደሆነ በውይይቱ ተነስቷል፡፡ በመምህራን ስልጠና ትልቅ አቅም ያለው እንዲሆን፣ የሬጅሰትራር አገልግሎት ፈጣንና የመማሪያ ክፍሎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ከጎንደር ዩኒቭርሲቲ ጋር አብሮ መስራት ይገባናል የሚለው ሀሳብ በጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በኩል ቀርቧል፡፡ በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀረቡት ሀሳቦች፣ የከፍተኛ ትምህርት የጥራት ችግሩ ከዩኒቭርሲቲዎችና ከኮሌጆች(ከሁለቱም) የሚከሰት መሆኑንና መገፋፋትም እንዳለ የተነሳ ሲሆን ችግሩን ለመቅረፍ ተደጋግፎ መስራት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ወደፊት በጋራ የሚሰራባቸው ጉዳዮች ተለይተው እስከሚቀርቡ ድረስም አብሮ መስራቱ እንደሚቀጥል በውይይቱ የማጠቃለያ ሀሳብ ላይ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን ከሌሎች የአውሮፓና አሜሪካ ሀገራት በጋራ እንደምንሰራው ሁሉ ከጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅም አብረን እንሰራለን በማለትና ስምምነቱ ፍሬያማ እንዲሆን መልካሙን ሁሉ ተመኝተው ውይይቱ ተጠናቋል
ዘጋቢ፡- በላይ መስፍን
የሕ/ዓ/አ/ግ/ዳይሬክቶሬት

