የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ የስርአተ-ፆታና ልማት ትምህርት ክፍል ለደባርቅ ወረዳ የባለድርሻ አካላት ስርአተ-ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ መስጠት በሚል ርእስ ዙሪያ የባለ ድርሻ አካላትን ግንዛቤ ለማሳደግ አላማ ያደረገ የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና መጋቢት 23 እና 24/2013ዓ/ም በደባርቅ ከተማ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በሀይድሮሊክና ውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ29ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ28ኛ ጊዜ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲአችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረውን የአለም የውሃ ቀን “ለውሃ ዋጋ እንስጥ” በሚል መሪ ቃል መጋቢት 22/2013 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል፡፡ የአለም …
በዓለም ለ110ኛ ጊዜ እና በሀገራችን ለ45 ጊዜ የተከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን መጋቢት 20/2013 ዓ.ም የሴቶችን እኩልነት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገነባለን በሚል መሪቃል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ለ5ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ካህሌ ጀንበሬ መርሀ-ግብሩን በንግግር …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚገኘው ፊዚክስ ት/ት ክፍል ከዚህ በፊት በጎንደርና አካባቢው ለሚገኙ ት/ቤቶች ለተግባርና ለሙከራ ትምህርት ግልጋሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በድጋፍ መልክ ማበርከቱንና የዘርፉ መምህራንም እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ ትምህርት ክፍሉ ለዩኒቨርሲቲው …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት “ውጤታማ የአሰለጣጠን ዘዴ” በሚል ርዕስ ዛሬ ማለትም መጋቢት 21/2013 ዓ.ም የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በአፄ ቴወድሮስ ግቢ T12 አዳራሽ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናውም ለ6 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚሰጠውም በጎንደር ዙሪያ በተመረጡ 6 ወረዳዎች ማለትም …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስነ-አእምሮ ትምህርት ክፍል መምህራንና የጤና ባለሙያዎች በጯሂት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋውያን ምንዱባን ማህበር ውስጥ ለሚገኙ የጤና መድህን ለተሟላላቸው 35 የአእምሮ ህሙማን መጋቢት 18/2013ዓ/ም ከቦታው ድረስ በመገኘት የበጎ ፈቃድ የአዕምሮ ህክምና እርዳታ …
በኢትዮጵያ የእንስሳት ሀኪሞች ማህበር አዘጋጅነት በአማራ ክልል በእንስሳት ህክምና ሙያ አዲስ የተመረቁ/ ስራ ፈላጊ ወጣቶች/፣ በመንግስት እንዲሁም በግል ፋርማሲ ወይም ክሊኒክ ስራ ላይ የተሰማሩ የእንስሳት ሀኪሞች መጋቢት 20/2013 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ጉብኝት አካሄዱ፡፡ የልምድ ልውውጡ Health …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን በወገራና በአርጫሆ ወረዳዎች በከብት ማድለብ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሴቶችና ወጣቶች በስራ ፈጠራ፣ በንግድ ስራ አመራር እንዲሁም በእሴት ሰንሰለት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈተቱት የኮሌጁ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ዶ/ር …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ 19 ክትባት ዛሬ ማለትም መጋቢት 20/2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሰጠት ጀመረ፡፡ በዚህ የመጀመሪያው ዙር የክትባት አሰጣጥ የተከተቡት የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ናቸው፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ በኮቪድ-19 ምክንያት ብዙ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል አዘጋጅነት “የዓባይ ውኃ ጉዳይ” በሚል መፅሐፍ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ኤፍሬም ጥሩነህ እንደገለጹት የአባይ ውኃ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳይ በመሆኑ ወርሃዊ መወያያችን በዓባይ ጉዳይ …
