ድካምዎ ፍሬ አፍርቶ ለሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ስለበቁ እንኳን ደስ አለዎት፡፡ የደንቢያው ቡቃያ ፣ በቆላድባና ጎርጎራ ትምህርት ቤቶች ተኮትኩተው፣ በአዲስ አበባው ኮከበ ጽብሃ በእውቀት ታንፀዋል፡፡ የያኔው እምቦቀቅላ ያሁኑ ፕሮፌሰር ንብረት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ሀዋሳ እርሻ ኮሌጅ ገብተው በእንስሳት እርባታና መኖ …
ለሙሉ ፕሬፌሰርነት ማዕረግ ስለበቁ እንኳን ደስ አለዎት! “አስተውሎ የሚራመድ ረጅም ርቀት ይጓዛል” የሚለው መርህ ብዙ ትምህርት ቤቶች ሰንደቅ ዓላማ መስቀያ ሰገነት ስር ተጽፎ አንብበን ይሆናል፡፡ ጥቂቶች ደግሞ በተግባር አሳይተውናል፡፡ ከጥቂቶቹ ውስጥ አንዱ ፕሮፌሰር ጋሻው አንዳርጌ ናቸው፡፡በፈተና ብዛት ያልወደቁ፣እንቅፋት አደናቅፎ ያልጣላቸው፣ችግር …
ባለፈው ግንቦት 13/2012 ዓ.ም በድንገተኛ ህሙማን ማከሚያ ክፍል ከተገኘው የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ጋር ንክኪ የነበራቸው የጤና ባለሙያዎች በሳይንስ አምባ ወሸባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡ ወገናቸውን በመርዳት ላይ የነበሩ ሰማንያ ስድስት (86) የጤና ባለሙያዎቻችን በአሁኑ ሰዓት ራሳቸውን ከቤተሰብ ለይተው ናሙና የሚወሰድበትን ቀን እየተጠባበቁ …
ለየጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳትና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቢሮ ጋር በመተባበር፣ ‘ኢሴንያ ፎኤቲዳ’ የተባለ አነስተኛ ነብሳት በመጠቀም፣ የዶሮ ምግብ ግብአቶችንና የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚችል አዲስ ቴክኖሎጂን ማላመድ ችለዋል፡፡ ኢሴንያ ፌኤቲዳ ከ580 – 710 ግ እምቅ ፕሮቲን፣ …
የዩኒቨርስቲያችን የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን የፊት ለፊት የማስተማር ዘዴ በኮረና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ግን የከፍተኛና ሳይንስ ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ዮኒቨርስቲው ተማሪዎቻችን ባሉበት ሆነው የሚማሩበትን ሂደት በመዘየድ የመማር ማስተማሩን ሂደት በጥሩ ጅማሮ በማስቀጠል ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም ቀድሞ በተቀመጠው የጊዜ …
ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከፌዴራል፣ አማራ ክልል እና ከዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ኮሮና ወረርሽኝን (COVID-19) ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራትን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ በአጠቃላይ ስፔሻላይድ ሆስፒታላችን የተዘጋጀውን የኮሮና በሽታ ማከሚያ ጣቢያ፣ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ክፍል እና የሳኒታይዘር ማምረቻ ማዕከልን ተመልክተዋል፡፡ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት ሲያገግሉ የነበሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር አንዳርጋቸዉ ጥሩነህ በደረሰባቸዉ አደጋ በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ግንቦት 7/2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ዶ/ር አንዳርጋቸዉ ጥሩነህ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት በህግ ማስተማር፤ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ደከመኝ ሳይሉ ሲያገለግሉ …
