ለየጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳትና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቢሮ ጋር በመተባበር፣ ‘ኢሴንያ ፎኤቲዳ’ የተባለ አነስተኛ ነብሳት በመጠቀም፣ የዶሮ ምግብ ግብአቶችንና የአፈር ለምነትን መጠበቅ የሚችል አዲስ ቴክኖሎጂን ማላመድ ችለዋል፡፡ ኢሴንያ ፌኤቲዳ ከ580 – 710 ግ እምቅ ፕሮቲን፣ …
የዩኒቨርስቲያችን የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን የፊት ለፊት የማስተማር ዘዴ በኮረና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ግን የከፍተኛና ሳይንስ ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ዮኒቨርስቲው ተማሪዎቻችን ባሉበት ሆነው የሚማሩበትን ሂደት በመዘየድ የመማር ማስተማሩን ሂደት በጥሩ ጅማሮ በማስቀጠል ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም ቀድሞ በተቀመጠው የጊዜ …
ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከፌዴራል፣ አማራ ክልል እና ከዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ኮሮና ወረርሽኝን (COVID-19) ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራትን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ በአጠቃላይ ስፔሻላይድ ሆስፒታላችን የተዘጋጀውን የኮሮና በሽታ ማከሚያ ጣቢያ፣ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ክፍል እና የሳኒታይዘር ማምረቻ ማዕከልን ተመልክተዋል፡፡ …
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት የእየሰራ የሚገኘው ›› የNala እና Jdc‹‹ ፋውንዴሽን የኮረና ቫይረስን ለመከላከል እንቅስቃሴ ከጀመረ አንድ ወር ተቆጥሯል፡፡ ፕሮጀክቱ ከንክኪ ነፃ የእጅ መታጠቢያ ታንከሮች ጀምሮ የቫይረሱን አስከፊነት በተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ እስከመፈጠር ድረስ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን በሬዲዮ፣ በዌብሳይትና በፌስቡክ አድራሻዎቻችን …
የዩኒቨርሲቲያችን አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ለሁሉም ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት አሰጣጥን በተመለከተ ዛሬ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ተማሪና መምህር ፊት ለፊት ተገናኝተው መማር ማስተማሩ ወደ ክፍል እስኪመለስ እና ከኮረና ቫይረስ (COVID-19) ስጋት ነፃ እስክንወጣ ድረስ የተስተጓጎለውን ትምህርት አማራጭ መንገዶችን ተጠቅሞ …
የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት ዓፀደወይን፣ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ጋሻው አንዳርጌ፣ቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር መሰረት ካሴ ፣አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ እንዲሁም የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህራን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት አቅራቢያ ከሰሞኑ በቁፋሮ የተገኘውን የጎረባ ጊዮርጊስ …
ከተማ አስተዳደሩ ዩኒቨርሲቲው የኮረና ቫይረስን ቀድሞ ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ከማድነቅም ባሻገር በሀገር ውስጥና በሀገር ውጪ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ግለሰቦችንና ባለሀብቶችን ለዚሁ ተግባር እንዲተባበሩ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ከሀገር ውጪ (ከዱባይ ሀገር) ከሚገኙ የጎንደር ከተማና አካባቢ ተወላጆች የተላኩትን 8 የሙቀት መለኪያዎች፣ …
የጎንደር ከ/አስተዳደር አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተቋቋመው አዲስ የኮቪድ-19 ህክምና መስጫ ማዕከል የ200 ሺ ብር ቁሳቁስ ድጋፍ ሚያዚያ 17/2012 ዓ.ም አበርክቷል፡፡ የተበረከተው ቁሳቁስ የውኃ ማሞቂያና ማቀዝቀዣ፣ፎጣ፣ጠረጴዛና የግድግዳ ሰዓት የሚያካትት ሲሆን በርክክብ ስነ ስርዓቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የጎንደር ከ/ አስተዳደር …
