የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አባላትና ሌሎች ተማሪዎች አገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ”Zoom Meeting” ቀጥታ በመቀላቀል ለመሳተፍ የኮኔክሽን መቆራረጥ ችግር ቢያጋጥማቸውም ” ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መርሃ ግብር ሰኔ 3/2013 ዓ.ም …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል ‹‹የገቢያ ትስስር ለእደ ጥበብ አምራቾች›› በሚል ርዕስ ለጎንደርና አዲስ ዘመን ከተማ የእደ ጥበብ አምራቾች፣ የገቢያና ንግድ ባለሙያዎች ዛሬ ሰኔ 4 እና 5 /2013ዓ/ም በማራኪ ግቢ አልሙኒየም ህንፃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን …
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር “Grand Challenge Ethiopia Orentation Workshop for University Researchers”በሚል የሀገሪቱን አበይት የጤና ችግሮች በምርምርና በፈጠራ ለመቅረፍ የሚያስችል አውደጥናት ሰኔ 3/2013 ዓ.ም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ተካሄደ። በአውደጥናቱ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ለአዲስ የፒ ኤች ዲ ተመራቂ ስታፍ አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ ፕሮግራም ሰኔ 03/2013ዓ.ም በማራኪ ግቢ አዘጋጀ። በፕሮግራሙ የዲፓርትመንቱን ኃላፊ አቶ እንደሰው እሸቴን ጨምሮ በርካታ የትምህርት ክፍሉ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡ትምህርት ክፍሉን የተቀላቀሉ …
የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ለማመንጨት በአፍሪካ በአንደኛነት ደረጃ በዓለም አቀፍ ደግሞ በ8ኛ ደረጃ የተቀመጠው የታላቁ የህዳሴ ግድብ በ2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ግድቡ 6000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ከ80% በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አሁን ላለባቸው የኤሌክትሪክ ሀይል እጦት መፍትሄ ይሆናል ተብሎ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በማዕከላዊ ጎንደር ፣በምዕራብ ጎንደርና በሰሜን ጎንደር ለሚገኙ የውኃ፣ የመንገድ ፣የኮንስትራክሽ፣የዲዛይን ባለሙያዎች፣አማካሪ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በተገኙበት “Application of Expanded Polystyrene /EPS/Geofoam in Civil Engineering Projects” በሚል ርዕስ ሰኔ 2 እና 3/2013 ዓ.ም በአጼ ፋሲል ግቢ የግንዛቤ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት አዘጋጅነት ’’ሀገር በቀል የትብብር ፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞች እና አካታች የምርምር ቡድኖች ’’ (Home- Grown Collaborative PhD Programs and 20 New Interdisciplinary Research Groups) በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አዲሱን ስትራቴጅክ እቅድ መሰረት ያደረገ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና የምርምር የትኩረት መስኮች መመሪያ ሰነድ ረቂቅ ግምገማ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ሰኔ 01 እና 2 /2013ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ በአውደ ጥናቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል የፍልስፍና ዶክትሬት ድግሪ በተግባራዊ ሥነ-ልሳን / Doctor of Philosophy in Applied Linguistics/ ለመክፈት ሀገር አቀፍ ካሪኩለም ግምገማ በማራኪ አልሙኒዬም አዳራሽ ግንቦት 27 /2013 ዓ.ም አካሄደ ፡፡ በዕለቱ ሀገር አቀፍ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል የመጀመሪያው የተሳካ ከፍተኛ የዳሌ አጥንት ስብራት ቀዶ ህክምና በውጪ በሚታሰር ብረት መከናወኑን የሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ት/ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ቃለአብ ገልፀዋል። በዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ በተመራ ቡድን ይህ መጀመሪያው የተሳካ ህክምና የተደረገው …



