በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፌደራሊዝምና ህገ-መንግስት ሀሳቦች ላይ ግንቦት 9/2013 ዓ.ም በማራኪ አሉምኒየም አዳራሽ ውይይት አካሄዱ፡፡ በውይይቱ የብልጽግና ፣አብን ፣ነፃነትና እኩልነት፣ አዴሀን፣መኢአድ፣እናት እና ህብር ዲሞክራሲ ኢትዮጵያ ፓርቲዎች ተወካዮች ፣ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን፣ ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሰራተኞች ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ሸቀጦችን ከሌሎች ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በመግዛት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ማህበሩ ሰራተኞች ያለባቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ እንዲችሉና በስራቸው ላይ ተረጋግተው እንዲሰሩ ለማስቻል የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱ ይታወሳል፡፡ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሀይል ምርምር ማዕከል (Energy Research Center) በማቋቋም የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በማዕከሉ የሚሰሩ ከዘርፉ ጋር የተያያዙ የሳይንሳዊና የዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እውቀቶችንና ልምዶችን ማስተዋወቅ ዓለማው ያደረገ አውደ-ጥናት ሚያዚያ 29/2013 ዓ.ም በኢንስቲቲዩቱ ዲን ህንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዲን …
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያና ከአለም አእምራዊ ንብረት ድርጅቶች ጋር በመተባበር በባህላዊ ህክምናና በአእምሯዊ ንብረት አጠባበቅ ዙሪያ ግንቦት 2 እና 3/2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡ በምክከር መድረኩ ከደቡብ አፍሪካና ከጀኔቫ ሀገራት የተለያዩ ምሁራን በበይነ መረብ ተሳትፈዋል፤ በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው የባህል …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የስትራቴጅክ እቅድን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከግንቦት 3-6/2013 ዓ.ም በጎንደር ኦሎምፒክ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከእያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምን እንደሚጠበቅ በማሳሰብ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም ማኔጅመንት የትምህርት ክፍል ሀገር በቀል እውቀቶችን በመጠቀም አዳዲስ የቱሪዝም መስኮችን የማጎልበትና የመፍጠር ንድፈ ሃሳብን በተመለከተ፣ ሀገር በቀል የስዕል አሳሳል ጥበብን፣ የብራና አዘገጃጀትና አጠቃቀምን እንዲሁም የሸክላ ሥራ ሙያዎችን በተመለከተ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ህይወት በጎአድራጎት ማህበር የተለያዩ በአላትን ከአረጋዊንንና አቅመ ደካሞች ጋር በማሳለፍና ነዳያንን በመደገፍ የተለያዩ መልካም ተግባራትን እንደሚያከናውን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የማህበር አባላት ከትንሳኤ አስከ ዳግማይ ትንሳኤ ያለውን ሳምንት በሆስፒታል ያሉ ህሙማንን እና በካለን ብናካፍል በጎአድራጎት ማህበር ያሉ ነዳያንን በመጎብኘት …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቅድመ ምረቃ የህክምናና ጤና ሳይንስ ፕሮግራሞች ሀገር አቀፍ የስርአተ ትምህርት ግምገማ አውደ ጥናት ( National Curriculum Evaluation and Harmonization Workshop For Undergraduate Medicine and health science programs) ሚያዚያ18 …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ በጎርጎራ የተቀናጀ የአትክልትና ፍራፍሬ ሰርቶ ማሳያ የተሰሩ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን በአርሶ አደሮች የመስክ ቀን ሚያዚያ 16/2013ዓ/ም ለተለያዩ አጋር አካላት አስተዋውቋል፡፡ በዕለቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ቢኒያም ጨቅሉ፣ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ Ethiopian Renaissance Journal of Social Science and Humanities (ERJSSH) የተሰኘውን የኮሌጁን ጆርናል ሂደት ግምገማ መርሃ- ግብር ሚያዚያ 15/2013ዓ/ም በማራኪ አልሙኒዬም ህንፃ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ ምርጥ ተማሪዎች፣ ምርጥ መምህራን፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ለጆርናሉ አስተዋፅዖ …
