በቱሪዝም እድገት ላይ ያተኮረ የስልጠናና የምክክር መድረክ ተካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት አማካኝነት በያዝነው የበጀት ዓመት የማህበረሰብ አገልግሎቶች ከዚህ ቀደም ተደራሽ ባልሆነባቸው ወረዳዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

እንደ ሚታወቀው ዩኒቨርሲቲያችን በዓይን ክህምና ዘመቻ፣ በነፃ ህግ አገልግሎት፣ በትምህርት፣ በግብርናው ዘርፍ፣ በቁሳቁስ ድጋፍ እና በሌሎች ዘርፎች እያደረገ ያለው ተሳትፎ ውጤታማ መሆኑ ይተወቃል፡፡
እንደ አብነትም በዚህ ዓመት በ230 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የበየዳ ወረዳን ጨምሮ በጃናሞራ፣ በዳባርቅ በዳባት፣ በበለሳ፣ በወገራ፣ በአዲስ ዘመን፣ በደንቢያ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በላይ አርማጭሆ እና በክልላችን ሥር በማግኙ ዞኖችና ወረዳዎች በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ጥር 20/2012 ዓ.ም በጃናሞራ ወረዳ መከነ-በርሃን ከተማ በቱሪዝም እድገት ላይ ያተኮረ የስልጣናና የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡ በስልጠናው ከወረዳው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች ወጣቶች፣ የንግድና ሆቴል ባለቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ስልጣናው በቱሪዝም ዕድገት ላይ የሚታዩትን ተግዳሮቶች መከላከል የሚያስችል እንደሆነ የጃናሞራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረበ መለሰ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡ የቱሪዝም አስፈላጊነትና ዓለማውን አስመልክቶ የወረደው ባህልና ቱሪዝም ኃላፊ አቶ አማረ ታደሰ ለተሳታፊዎች አያቀረቡ ሲሆን፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ እንግዱ ገብረ ወልድ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ እየተጋረጠ ያለውን አደጋ፣ የቱሪዝም እድገት ማነቆዎችና መድረግ ስለለባቸው የመፍትሄ ሃሳቦች አብራርተዋል፡፡

ይህ ስልጠና የአፄ ቴዎድሮስ 165ኛ ዓመቱን የንግስ በዓል በየካቲት ወር ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለማጠናከር የሚያግዝ ሲሆን የወረዳው ተወላጅ የሆኑት አቶ በያብል ሙላቴ የደረሰጌ ማርያምን ገዳም በጥናት ላይ ተመሰርተው ትክክለኛውን ታሪክ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ በመድረኩ በርካታ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን በጨረሻም ከቤቱ መለስ ተሰጥቶና መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



