በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኮረና ተሕዋስን ለመከላክል የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ዩኒቨርሲቲያችን ›› ከNala እና Jdcy‹‹ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ያለ ሲሆን፣ የኮረና ተሕዋሲን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ከንክኪ ነፃ የሆኑ የእጅ መታጠቢያ ታንከሮችን ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢ በማስቀመጥ፣ የተሕዋሲያኑን መተላለፊያና መከላከያ መንገዶችንና ምልከቶችን በትልልቅ ባነሮች ላይ በማሳተምና በሚታዩ ቦታዎች ላይ በመስቀል እንዲሁም ፊት ለፊት በማስተማር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ሚያዝያ 8/2012 ዓ.ም ተህዋሲያኑን ለመከላከል ተመሳሳይ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን በአጠቃላይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 19 ከንከኪ ነፃ የሆኑ ለእጅ መታጠቢያ የሚያገለግሉ የውሃ ታንከሮችና 19 ትምሕርት ሰጭ ባነሮች በቅዳሜ ገቢያ፣ በአራዳ፣ በቦሌ ጤና ጣቢያ፣በአድባባይ እየሱስና በቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያናት፣በከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ በፒያሳና በሆስፒታል አካባቢዎች እንዲቀመጡ መደረጋጀውን ዶ/ር መኩሪያው ዓለማየሁ ገልጸዋል፡፡

የሕዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



