የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች አተገባበርን በተመለከተ ከዳይሬክቶሬቱ የተሰጠ አቅጣጫ
የዩኒቨርስቲያችን የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን የፊት ለፊት የማስተማር ዘዴ በኮረና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ግን የከፍተኛና ሳይንስ ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ዮኒቨርስቲው ተማሪዎቻችን ባሉበት ሆነው የሚማሩበትን ሂደት በመዘየድ የመማር ማስተማሩን ሂደት በጥሩ ጅማሮ በማስቀጠል ላይ ይገኛል፡፡
ለዚህም ቀድሞ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ (Calendar) መሰረት የሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት “Microsoft 365” ን በመጠቀም እና የመመሪያ ቁሳቁሶችን በኢሜል፤ በቴሌግራም፣ በሚሴንጀርና መሰል አማራጮችን ተጠቅሞ በመላክ ትምህርቱን ከቆመበት ማስቀጠል ተችሏል፡፡
መምህራን እና ተማሪዎች ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከአይ.ሴ.ቲ ዳይሬክቶሬት ተቋማዊ ኢሜል (Institutional ID) በትምህርት ክፍል ሃላፊዎች በኩል ያልወጣላቸውን ቶሎ በማውጣት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቶች እንዲጠናቀቁ በታላቅ አክብሮት እያሳሰብን የፒ.ኤች.ዲ ሴሜናሮች (PhD Seminars & PhD Weeks) እና ፈተናዎች (PhD Defense)፤ የሁለተኛ ድግሪ ተመራቂዎች የሙከራ ፈተናዎች (Mock Defense) እና የመመረቂያ የምርምር ፈተናዎች (Final Defense) በተቀመጠላቸው የግዜ ሰሌዳ መሰረት በ”Microsoft 365″ አማካኝነት የሚካሄዱ ይሆናል፡፡
ስለሆነም ተማሪዎች የተላለፈውን ውሳኔ በማጤን ከመምህራኖቻችሁ ጋር በቀጥታም ሆነ በተወካዮቻችሁ በኩል በመገናኘት ትምህርታችሁንም ሆነ የምርምር ስራችሁን በቴክኖሎጂ ተደግፎ እንድታጠናቅቁ የድህረ ምረቃ ኘሮግራሞች ዳይሬክቶሬቱ በድጋሚ ለማሳሰብ ይወዳል፡፡
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትግንቦት 10/2012 ዓ.ም



