የዩኒቨርስቲያችን ከፍተኛ አመራሮች በሳይንስ አምባ ወሸባ የገቡ የጤና ባለሙያዎችን ጎበኙ
ባለፈው ግንቦት 13/2012 ዓ.ም በድንገተኛ ህሙማን ማከሚያ ክፍል ከተገኘው የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ጋር ንክኪ የነበራቸው የጤና ባለሙያዎች በሳይንስ አምባ ወሸባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

ወገናቸውን በመርዳት ላይ የነበሩ ሰማንያ ስድስት (86) የጤና ባለሙያዎቻችን በአሁኑ ሰዓት ራሳቸውን ከቤተሰብ ለይተው ናሙና የሚወሰድበትን ቀን እየተጠባበቁ ነው፡፡

እነኝህ የስፔሻላይዝድ ሆስፒታላችን ሰራተኞች የስነ ልቦና ጥንካሬያቸውን አሳድገው ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደሚመለሱ ይታመናል፡፡ በስፍራው ተገኝተው ያሉበትን ሁኔታ የተመለከቱት የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮችም በክስተቱ መደናገጥ እንደማይገባ ከባለሙያዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



