‘አረንጓዴ አሻራ’ ን የማስቀመጥ ስራ ተሰራ
የደን ሀብት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግም ሆነ የአየር ንብረት ለውጡ የሚያስከትለውን ችግር ለመቅረፍ ያለውን ጉልህ ጠቀሜታ ተከትሎ፣ ባለፈው አመት በአዲስ መነሳሳት የተጀመረው ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› በኢትዮጵያ የደን ሀብትን በማበልፀግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡

በተመሳሳይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ከአካባቢ ጥበቃና ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጋር የተያያዙ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያክል በ“አልጣሽ” ብሄራዊ ፓርክ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችንና ምቹ አጋጣሚዎችን በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር አጉልቶ በማሳየት በኩል የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፤ በስሜን ተራሮችና በአማራ ሳይንት ወረሂመኑ ብሄራዊ ፓርክ ቀላል እማይባሉ ስራዎችንም እየሰራ ይገኛል፡፡ የበርካታ እምቅ (ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ) ሀብት ባለቤት የሆነው ‘ጣና’ን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለመታደግ በዩኒቨርሲቲው ምሁራን በኩል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ጊዜ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ዛሬ ሰኔ 17/2012 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው በ2012 ዓ.ም ለመትከል በእቅድ ከያዘው ከ60,000/ስልሳ ሺ/ ችግኞች መካከል በማራኪ ክ/ ከተማ አይራ ከተዘጋጀው 32000 የችግኝ መትከያ ጉድጓድ መካከል በአየር ንብረት ለውጥ ምርምር ቢሮ አስተባባሪነት 3_000 ችግኞች ለመትከል ተችሏል። በችግኝ ተከላውም የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይንና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የጸጥታ አካላት ናቸው። በዚሁ አካባቢ ባለፈው ዓመት 12, 500(አስራ ሁለት ሺ አምስት መቶ) ችግኖች ተተክለው በአሁኑ ጊዜ ጥሩ እሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የዘመቻው አስተባባሪ ዶ/ር ኢብራሂም ኢሳ ገልጸዋል፡፡

በሚቀጥሉት ቀናት ደግሞ ተጨማሪ ሰላሳ ሺ ችግኖችን በዩኒቨርሲቲው ግቢዎች ውስጥ ለመትከል እንደታቀደም ዶ/ር ኢብራሂም አያይዘው ገልጸዋል፡፡አንዳንድ ያአነጋገርናቸው የዘመቻው ተሳታፊዎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ስራ አስፈላጊነት ገልጸዋል፤ ችግኞችን መትከል ብቻ በራሱ ውጤታማ እንደማያደግ በማሳሳብ በቂ ክትትል እንዲደረግለቻው በአንክሮ ተናግረዋል፡፡
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!የጎንደር ዩኒቨርሲቲ!

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



