የተማሪዎቻችን ምርቃት በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ያላያችሁ የገፃችን ተከታዮች እነሆ ትውስታ
ከቀረ ያረፈደ ይሻላል ነውና ባለፈው ሐምሌ 04/2012 ዓ.ም በድምቀት ያካሄድነው የብይነ መረብ (virtually ) የተማሪዎች ምረቃ መርሃ ግብርን እናስታውሳችሁ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የፊት ለፊት ትምህርት ቢቋረጥም በቴክኖሎጂ ታግዞ የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ማስተማሩና ለምረቃ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም ኮርሶች አጠናቀው የመመረቂያ ፕሮጀክት በመስራት ላይ የነበሩ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችንም የተግባርና የወረቀት ምርምሮቻቸውን እንዲያጠናቅቁ በማድረግ አስመርቋል፡፡
ይህ በታሪክ አጋጣሚ የተከሰተ ሁናቴ የተማሪዎቻችን የምርቃት ደስታ እንዳያደበዝዘው ተቋማችን የቴክኖሎጂ አቅሙን ተጠቅሞ ባማረ መልኩ አካሂዷል፡፡ የምርቃት ሥነ ስርዓቱ በሰዓቱ በአማራ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሽፋን የነበረው ቢሆንም የመመልከት ዕድሉ ላልተመቻችሁ የደስታ ድባቡ ውብና ማራኪ እንደነበር እናበስራለን፡፡
በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሐምሌ 18/2012 ዓ.ም








