የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለጎርጎራ ልማት ለመለገስ ወሰኑ
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “ገበታ ለሃገር” ጥሪ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ይፋ ከሆኑት ፕሮጀክቶች ቀዳሚዋ ጎርጎራ ነች፡፡

የጎርጎራን ልማት እውን ለማድረግ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመለገስ ወስነዋል፡፡

ከሁሉም የዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብ ጋር ተመካክረን እንዳቅማችን ለማበርከት በየግቢዎችና ኮሌጆች ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

በመሆኑም የቻልነውን አስተዋጽኦ አድርገን የጎርጎራን ትንሳኤ እንድናበስር ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡ ሀገራችን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!



