በጎንደር ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እንደገና ለመቀበል የተደረጉና እየተደረጉ ያሉ ዋና ዋና ዝግጅቶች
1. የኮቪድ 19 ኘሮቶኮልን ተከትሎ የመኝታ ቤቶች፣ የመመገቢያ ቤቶች፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራዎች እና ላውንጆች አገልግሎት እንዲጀምሩ ዝግጅት ተደርጓል። የተማሪ ጥምርታ በዶርም፣ በመመገቢያ አዳራሽ፣ በክፍል፣ በቤተ መጻሕፍት እና በቤተ ሙከራዎች ተወስኗል፣
2. በለይቶ ማቆያነት ሲያገለግሉ የነበሩ ህንጻዎች ጸረ ቫይረስ ኬሚካል እርጭት እና ጽዳት ማድረግ፣
3. የምግብ ግብዓቶች እና ቁሳቁስ ማሟላት፣
4. የተጓደሉ የአስተዳደር ሠራተኞች ማሟላት፣ ትውውቅና ስልጠና፣
5. የተለያዮ ህንፃዎች ጥገናና ቀለም ቅብ ሥራ፣
6. አስተማማኝ የውሐ እና መብራት አቅርቦት እንዲኖር የመስመሮች ጥገና ማድረግ እንዲሁም ከከተማ አስተዳደራችን የመብራት እና ውሃ አገልግሎቶች ጋር በጋራ እየሠራን መሆኑ፣
7. ከንክኪ ውጭ (በእግር የሚከፈቱ) መታጠቢያ ገንዳዎች፣ ማስክና ሳኒታይዘር ማምረት፣
8. ከተማሪ አገልግሎቶች ጋር በቀጥታ ከሚያገናኙ ክፍሎች ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን የዝግጅትና ግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ፤
9. ከተማሪዎች ጋር ፊት ለፊት አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች የተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ፣
10. የጸጥታ እና የኮቪድ 19 ልዮ እቅዶች ዝግጅትና ትውውቅ፣
11. የኮቪድ 19 የትምህርትና ግንዛቤ ፈጠራ ሰነዶች፣ ባነር፣ በራሪ ወረቀቶች፣ የሥነ ምግባር ደንብ እና ሌሎች መመሪያዎች ሕትመቶች ሥራ፣
12. ከዮኒቨርሲቲያችን ማሕበረሰብ የተማሪ አደረጃጀቶችን ጨምሮ፣ ከከተማ አስተዳደርና ጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና ከተለያዮ ጸጥታ አካላት የተውጣጡ የተለያዮ ኮሚቴዎችን ማቋቋም (የሰላማዊ መማር ማስተማር ጥምር ኮሚቴ፣ የጸጥታ ኮሚቴ፣ የተማሪ ቅበላ ኮሚቴ፣ የክትትልና ድጋፍ ኮሚቴ)። የተማሪ ሕብረት አባላት ቀድመው እንዲገቡ ይደረጋል፣
13. የተማሪዎቻችን መግቢያ ጊዜ ጨምሮ የአመቱ አካዳሚክ ካሌንደር ተዘጋጅቷል፣
14. የኮቪድ 19 ተጠርጣሪዎች ማቆያ እና ማከሚያ ማዕከላቶቻችን ማጠናከር እንዲሁም የሕክምና ግብዓት ማሟላት፣
15. የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ተሠርቷል። እንዲሁም በ2013 የትምሕርት ዘመን በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት የዮኒቨርስቲው የተለያዮ ኃላፊዎች እና ፈጻሚ አካላት በተገኙበት መገምገሙከዋና ዋናዎቹ ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ።
የሣይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን ያደረግነውን ዝግጅት ገምግሞ የሚሰጠንን ግብረ መልስ አካተን ከጨረስን በኋላ የተማሪዎቻችን መግቢያ ጊዜ በቅርቡ የምናሳውቅ በመሆኑ ውድ ተማሪዎቻችን በትዕግስት እንድትጠባበቁን በዚሁ አጋጣሚ ከአክብሮት ጋር አሳስባለሁ።



