አስደሳች ዜና
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርጥ ዓለም ዓቀፋዊ ዩኒቨርሲቲ (Best Global University) ምድብ ውስጥ ተካተተ፡፡ከ30 ዓመት በላይ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎችን ደረጃ በማውጣት የሚታወቀው “usnews & world report” በቅርቡ በ81 ሐገራት በጀመረው የትምህርት ተቋማት ጀረጃ አሰጣጥ መሠረት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከምርጥ 1500ዎቹ ውስጥ ተካቷል፡፡ ደረጃውም ከዓለም 826ኛ፣ ከአፍሪካ 20ኛ፣ ከኢትዮጵያ 2ኛ ሆኗል፡፡ “usnews & world report” ደረጃውን ያወጣው 13 የተለያዩ መመዘኛ መስፈርቶች በመጠቀም ነው፡፡ለመላው የዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብና አጋሮቻችን እንኳን ደስ አለን እያልን ከዚህ የተሻለ ለመሆን ጠንክረን እንስራ የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡መረጃውን በድህረ ገፅ ለማየት ( https://www.usnews.com/…/university-of-gondar-529442 ) ይጫኑ፡፡ሀገራችን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!**************************************
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም




