በቴክኖሎጂ ሽግግር ፕሮጀክት የተሰሩ የምርምር ውጤቶች ወደ ምርት መገባት ጀምረዋል
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የቴክኖሎጂ ሽግግር ፕሮጀክት አካል የሆኑ 16 የምርምር ውጤቶች መኖራቸውን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕ/ር መርሻ ጫኔ ዩኒቨርሲቲው ካገኛቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች መካከል አንዱ የሆነው ከንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ ለዩኒቨርሲቲው ግቢዎችና ከግቢ ውጭ ላሉ ድርጅቶች እንዲሁም ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚሆኑ ምርቶችን ከነሃሴ 2012 ዓ.ም ጀምሮ እያመረተ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን ከንክኪ ነፃ የሆኑ 99 የእጅ መታጠቢያዎችን፣ 100 ቋሚ የፈሳሽ መድሃኒት መስጫ መሳሪያ ( IV stand) ፣ የመኪናና የቤት በር መክፈቻዎችና የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከላይ የተገለጹትን እና ሌሎች የቴክኖሎጅ ሽግግር ውጤት የሆኑ ምርቶችን ለማውጣት ከ24 በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም የፕሮጀክቶቹ አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር አሸናፊ ተስፋየ ገልጸዋል፡፡ሀገራችን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!********************************************************
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት





