ኮፊ ኮሪያ የተሰኘው ግብረሰናይ ደርጅት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናከረ
በኢትዮጵያ (የKOFIH) ዓለም አቀፍ የጤና ፋውንዴሽን ዳይሬክተር) ሚስተር ዶንግሁንግ ካንግ በደቡብ ኮሪያ የሚገኘውን ታዋቂውን የባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ድርጅትን በብቸኝነት ወክለው የተገኙ ሲሆን፣ ጥቅምት 12/2013 ዓ.ም የጎንደር ዩኒቨርስቲን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ቀጣይ የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል፡፡
በውይይቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን ፣ የአስተዳደር ም/ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጋሻው አንዳርጌ ፣ የሕክምንን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ዳይሬክተር ዶ/ር አስማማው አጥናፉ ፣ አጋርነቱን የፈጠሩት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የባዮሜዲካል ኢንጂነርኢንግ አቶ ብሩተስፋ ሙሃባው ፣ ከ KOFIእና ከጤና ሚኒስቴር የመጡ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡የውይይቱ ዋና ርዕሰ ጉዳይ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የባዮሜዲካል ምህንድስና ላይ “የህክምና መሳሪያዎችን ሲስተም ማጠናከር” የሚል የጋራ ፕሮጀክት ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በ 3 ዘርፎች የተከፋፈለ ሲሆን የባዮሜዲካል መሐንዲሶች ማሽኖችን የሚያስተናግዱበት ቦታ መስጠት፣ ሂደቱን የጠበቀ ትንታኔ ማቅረብና በማሽኖቹ ላይ ስልጠና መስጠት ናቸው፡፡
በመጨረሻም ተሳታፊዎች ይህ ዓነቱ የትብብር ሥራ በቀጣይ የበለጠ እንደሚያስፈልግ እና ከ KOFIH ጋር ያለው ግንኙነትም አዳዲስ እውቀቶችን በመጨመር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ ተደርሶ ፕሮግራሙ ተናጠናቋል፡፡
ሀገራችን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
********************************************************
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 12/2013 ዓ.ም





