በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (STEM) ማዕከል ወቅታዊ ችግርን የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎች ለተለያዩ አካላት ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም ለእይታ ቀርበዋል፡፡
የማዕከሉ አስተባባሪ የሆኑነት አቶ ግርማ ወርቄ እንደገለጹት ፈጠራ ስራዎቹ የተሰሩት በጎንደር ዩኒቨርሰቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል እገዛ በሚደርግላቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን ፈጠራዎቹ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ናቸው፡፡ ከማንኛውም ንክኪ ነጻ የሆነ እና የእጅ ማድረቂያ ያለው የእጅ መታጠቢያ (No touch hand wash with drier)፣ የአንበጣ መንጋ ወደ ውስጥ በመሳብ የሚያስወግድ (locust Trap) እና የበሽተኞች የህክምና አገልግሎት መስጫ/ መተግበሪያ (Patient management system) በተማሪዎች ተሰርተው ለእይታ ከቀረቡት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡
በዕለቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔ እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (STEM) ማዕከል ይህ የፈጠራ ስራ መሰራቱ የሌሎች ተመሳሳይ ማዕከላት ተማሪዎች ድብቅ የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲጠቀሙበት ጥሩ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
*******
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት





