ማስታወቂያ ለ2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
ደረጃ ዶትኮም ለ 2013 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ቨርቹዋል የስራ አውደ ርዕይ ሲያዘጋጅ መቆየቱ ይታወሳል::
በመሆኑም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የውጤታማ ትግበራ ክፍል የተማሪዎቸ ስራ ተኮር ማማከርና ፈጠራ ማዕከል በጠየቀው መሰረት የዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂ ተማሪዎቻች ታህሳስ 9 እና 10, 2013 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ቨርቹዋል አውደ ርዕዩ ላይ እንዲሳተፉ እንጠይቃለን::
ለመመዝገብ እና የስራ አፈላለግ ስልጠናውን ለመውሰድ የምትፈልጉ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን መመዝገብ ትችላላችሁ
የስራ አፈላለግ ስልጠና ቀን ታህሳስ 3 እስከ 7 2013, ዓ.ም
የስራ አፈላለግ ስልጠና ሠዓት
– ከጠዋቱ 3:00 – 5:00
– ከጠዋቱ 5:00 – 7: 00
– ከቀኑ 7:00 – 9:00
– ከቀኑ 9:00 – 11:00
ለበለጠ መረጃ
+251 966081024 (ደረጃ ዶት ኮም)
+251960100825(Dr. Asmamaw Z.-የጎንደር ዩኒቨርሲቲ)
ቴሌግራም @AskDereja @DerejaOfficial




