“የዓባይ ውኃ ጉዳይ” በሚል መፅሐፍ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል አዘጋጅነት “የዓባይ ውኃ ጉዳይ” በሚል መፅሐፍ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ኤፍሬም ጥሩነህ እንደገለጹት የአባይ ውኃ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳይ በመሆኑ ወርሃዊ መወያያችን በዓባይ ጉዳይ መፅሐፍ ላይ በመሆኑ ጠቃሚ መረጃዎችን የምናገኝበት ስለሆነ መልካም የውይይት ጊዜ ይሁንልን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“የዓባይ ውኃ ጉዳይ” መፅሐፍ ደራሲ ዶ/ር ተፈሪ መኮነን በበኩላቸው መፅሐፉ በአባይና ገባር ወንዞቹ፣ በአባይ ጉዳይ ስላሉት ፍጥጫዎች፣ አለመግባባቶችና በሀገራችን ላይ የሚፈጠሩት ጫናዎችና ምክንያታቸውን፣ አውሮፓውያንና አሜሪካ በአባይ ውሃ ጉዳይ ምን ማድረግ ችለዋል፣ በ1959 በግብፅ፣ በሱዳንና በእንግሊዝ መሃል የተፈረመን የአባይ ስምምነት ግብፅ አትንኩብኝ የማለቷ ሚስጥርና ውዝግቦችን በሚገባ የያዘ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ውይይቱ በማራኪ ግቢ የተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት በተገኙበት በ17/7/2013 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡





