ከአማራ ክልል የተውጣጡ የእንስሳት ህክምና ባለሙያዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ
በኢትዮጵያ የእንስሳት ሀኪሞች ማህበር አዘጋጅነት በአማራ ክልል በእንስሳት ህክምና ሙያ አዲስ የተመረቁ/ ስራ ፈላጊ ወጣቶች/፣ በመንግስት እንዲሁም በግል ፋርማሲ ወይም ክሊኒክ ስራ ላይ የተሰማሩ የእንስሳት ሀኪሞች መጋቢት 20/2013 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

የልምድ ልውውጡ Health of Ethiopian Animals For Rural Development /HEARD/ በሚባል ፕሮጀክት ድጋፍ አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን የጉብኝት ዋና አላማ የእንስሳትን ጤና ለማሻሻል፣ ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም የግብይት ሰንሰለትን ለማሳደግና ለማሻሻል፣ የባለሙያዎችን እውቀትና ክህሎት ለማዳበር እንደሆነ የእንስሳት ህክምና ባለሙያና የጉብኝቱ አስተባባሪ ዶ/ር ገዋዶ አይሌዶ ተናግረዋል፡፡ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች አዲስ በመሰራት ላይ ያለውን የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ማስተባበሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፣ የወተት ከብትና የዶሮ እርባታ ማዕከላትን የጎበኙ ሲሆን በልምድ ልውውጡ ብዙ በተግባር የተደገፉ ልምዶችን እንዳገኙና እንደተደሰቱ አስተያየታቸውን ገልፀዋል፡፡




