በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ
በዓለም ለ110ኛ ጊዜ እና በሀገራችን ለ45 ጊዜ የተከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን መጋቢት 20/2013 ዓ.ም የሴቶችን እኩልነት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገነባለን በሚል መሪቃል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ለ5ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ካህሌ ጀንበሬ መርሀ-ግብሩን በንግግር ሲከፍቱ የቤት ውስጥ ስራን በእኩልነት በመስራት የመረዳዳት ባህልን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም ከቤቱ እንዲጀምር ቃል በመግባት ቀኑን ማክበር አለበት ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ በጠዳ ቀበሌ የሚገኙ ፋሲል የህፃናት የባህል ውዝዋዜ ቡድን አባላት በዓሉን አስመልክቶ ውዝዋዜ እና አስተማሪ ድራማ በማቅረብ ታዳሚውን አዝናንተዋል፡፡ በተጨማሪም በኮሌጁ በስራቸው ታታሪ የሆኑ ሰራተኞች የህይወት ተሞክሯቸውን አጋርተዋል፡፡
በመጨረሻም በተመደቡበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ለሆኑ ሴት መምህራን፣ ሴት ኮከብ ሰራተኞች እንዲሁም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበች ሴት ተማሪ የብርቱዋ ሴት ሽልማት በሚል የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡




