የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኬምስትሪ ት/ክፍል የ3ኛ ዲግሪ የስርዐተ- ትምህርት ግምገማ (curriculum review) እያካሄደ ነው፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም ኮሌጃቸው በውስን የሰው ሀይልና ትምህርት ክፍሎች ተማሪ ተቀብሎ ማስተማር እንደጀመረ እና በአሁኑ ወቅት በርካታ መምህራንና ተመራማሪዎች (በ2ኛና በ3ኛ ዲግሪ) አያሌ ተማሪዎችን በተለያዩ ኮሎጆች እያስተማሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

መርሀ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ በበኩላቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሆኖ መመረጡን አውስተዋል፤ ስለሆነም የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ስታንዳርድ ሊያሟሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በተለይም በ3ኛ ዲግሪ የትምህርት መርሀ ግብሮች የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሚሰራም ተናግረዋል፡፡

በስርዐተ-ትምህርት ግምገማው ጎንደር ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የዘርፉ ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ይህ ፕሮግራም ዛሬ የካቲት 10/2013 ዓ.ም ማምሻውን ይጠናቀቃል፡፡




