ከጫትና ከአደንዛዥ እፆች ነፃ የሆነ ትውልድ ለማፍራት የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት መጋቢት 2 እና 3 / 2013 ዓ.ም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ ግለሰቦች በጯሂት ከተማ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡

የስልጠናው አስተባባሪ እና በፋርማሲ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ እሸቴ መለሰ እንደገለፁት አደንዛዥ እፆችን መጠቀም ማህበራዊ ጉዳትን የሚያስከትል በመሆኑ የዛሬው ስልጠና ለጯሂት አካባቢ ነዋሪዎች የጫት መቃም ጎጅነቱን በማሳዬት ህብረተሰቡ ለጉዳዩ ትኩረት ሠጥቶ እና እርስ በእርስ ተደጋግፎ ይህን አስከፊ ሱስ ለማሰወገድ ሞዴል ወጣቶችን በመፍጠር አርያነት ያለው የመከላከል ስራ ለመስራት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

የጫት ሱስ በጥቂት ሰዎች እና በአጫጭር ስልጠና ብቻ መከላከል የሚቻል ባለመሆኑ ሁሉም የህብረሰተብ ክፍል ሊሳተፍበትና ግንዛቤ በመፍጠር ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የመከላከል ስራ ሊሰራ ይገባል በማለት አስረድተዋል ፡፡




