ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን ስልጠና ተሰጥቷል
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከመማር ማስተማር በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞችና ከዩኒቨርሰቲው ውጪ ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከኮምፒዩተር ጋር የተያያዙ በርካታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡


በተመሳሳይ በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖን ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን መሰረታዊ የኮምፑዩተር ትስስር ክህሎት (Basic Computer Networks Related Skills) እና ኢ- ለርኒግ ሲስተምስ (e-learning systems) ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ከመጋቢት 3-4/2013 ዓ.ም በኮሌጁ አይሲ.ቲ ላቦች (መማሪያ ክፍሎች) መሰጠት ጀምሯል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ዲን አቶ ቴወድሮስ አለሙ ስልጠናውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት፣ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀትና ክህሎት እድሉን ላላገኙ የሙያ አጋሮቻቸው እንዲያጋሩ አሳስበዋል፡፡ መሰል ስልጠናዎችም በሌሎች አካባቢዎች ሙያተኞች እንደሚሰጥ አቶ ቴወድሮስ አያይዘው ተናግረዋል፡፡




