የችግር ትንተና እና ስልታዊ የአፈታት ሂደት በሚል ስልጠና መስጠት ተጀመረ!
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም በችግር ትንተና እና ስልታዊ የአፈታት ሂደት / strategic problem analysis and solving /በሚል ርዕስ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጤና ባለሙያዎችና አመራሮች ከታህሳስ 19/2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በማክሰኝት ከተማ ተጀመረ ፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና አጠ/ስፔ/ሪፈራል ሆስፒታል አካዳሚክ ዳይሬክተር ዶ/ር አስማማው አጥናፉ እንደገለፁት በበርካታ ቦታዎች ላይ ያሉ ባለሙያዎች የተቋማቸውን ችግሮች ስልታዊ በሆነ መልኩ ለመለዬት እና በአግባቡ መፍታት እንዲችሉ ለማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ ከስልጠናው በኋላ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን የመቅረፅ አቅም የስልጠናው ተሳታፊዎች እንዲያዳብሩ እንደሚረዳ እና ባለሙያዎችም ሆኑ አመራሩ በደራሽ ስራ ታጥረው ከመዋል ወጥተው ተቋማትን በታቀደላቸው እቅድ መሰረት ችግሮቻቸውን እየፈቱ መስራት እንዲችሉ ስልጠናው አጋዥ መሆኑን ደ/ር አስማማው ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና አጠ/ስፔ/ ሪፈራል ሆስፒታል የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሪት ቤተልሄም አንተነህ በበኩላቸው ስልጠናው ያተኮረው የችግር ትንተና እና ስልታዊ የአፈታት ሂደት ላይ ሲሆን፣ ከስልጠና በኋላም በወረዳዎች እየተገኙ አፈፃፀሙን እንደሚከታተሉ አስገንዝበዋል ፡፡
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
ታህሳስ 19/2013 ዓ.ም







