የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የጤናው ዘርፍ አጋር አካላት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የጤናው ዘርፍ አጋር አካላት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ የህክምና መስጫ ክፍሎችን ማለትም የኩላሊት ህክምና ማእከሉን ፣የሪፈራል ሆሰፒታሉን እና የድንገተኛ ህክምና ክፍሎቹን ነሀሴ 25/2011 ዓ.ም ጎብኝተዋል፡፡

የጉብኝቱ ዋና አላማ የሆስፒታሉን አጠቃላይ አሰራርና ህክምና አሰጣጥ በመመልከት፣ችግሮቹን መለየትና መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት መሆኑን የህከምናና ጤ/ሳ/ኮሌጁ እና የአጠቃላይ ስፔ/ሆስፒታሉ አካዳሚክ ዳይሬክተር ዶ/ር አስማማው አጥናው ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱም በተለይ የሆስፒታሉ የጤና መረጃ ልውውጥ የልህቀት ማዕከል ፣ዲጅታል የታካሚዎች መዝገብ እና የመድሀኒት ቅመማ ክፍል፣ምቹ ኪሊኒክ፣የካንሰር ህክምና እና የኩላሊት እጥበት ማዕከላት እንዲሁም የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍሎች ታይተዋል፡፡

ከፍተኛ አመራሮቹ እና አጋር አካላቱ ከጉብኝቱ ምርጥ ተሞክሮ ይሆናሉ ያሏቸውን አሰራሮች አድንቀዋል፤መስተካከል ያለበትንም ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም በአጠቃላይ ስፔ/ሆስፒታሉ አሰራር እና ህክምና አሰጣጥ ላይ እንቅፋት እየሆኑ ያሉ ሁኔታዎች በሆስፒታሉ አመራሮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የህ/ዓ/አ/ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



