በ 5 ዙር ያለ ምንም ክፍያ ሲሰጥ የነበረው መሰረታዊ የኮምፒዩተር ዕውቀትና ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቢሮ ከዩኒቨርሲቲው ኢንፎርማቲክስ ፋካሊቲ ጋር በመተባበር የዲጅታል ሊትሬሲ (መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትና ክህሎት) ስልጠና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሙያተኞች ከሀምሌ 29/2011 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዙሮች ያለ ምንም ክፍያ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ የመጨረሻው ዙር ሰልጣኞች ትላንት ጳጉሜ 1/2011 ዓ.ም ስልጠናቸውን ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

በስልጠናው የተሳተፍት የህብረሰሰብ ክፍሎች ዩኒቨርሲቲው ከክፍያ ነጻ የሆነ የዲጅታል ሊትሬሲ ስልጠና አዘጋጅቶ ከቴክኖሎጅ ጋር እንዲተዋወቁ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ለወደፊት ቢስተካከሉ ያሏቸውን ምክረ-ሀሳቦች ለፕሮግራሙ አዘጋጆች ተቁመዋል፡፡

የሚመለከታቸው አካላትም በተሳታፊዎችና በዘርፉ ሙያተኞች የተሰጡትን አስተያየቶችና ጥቆማዎች ለወደፊት ለማስተካከል ቃል ገብተው፣ መሰል ስልጠናዎች በስፋትና ረዘም ላለ ጊዜ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል፡፡

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



