በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት “ውጤታማ የአሰለጣጠን ዘዴ” በሚል ርዕስ ዛሬ ማለትም መጋቢት 21/2013 ዓ.ም የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በአፄ ቴወድሮስ ግቢ T12 አዳራሽ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናውም ለ6 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚሰጠውም በጎንደር ዙሪያ በተመረጡ 6 ወረዳዎች ማለትም …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስነ-አእምሮ ትምህርት ክፍል መምህራንና የጤና ባለሙያዎች በጯሂት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋውያን ምንዱባን ማህበር ውስጥ ለሚገኙ የጤና መድህን ለተሟላላቸው 35 የአእምሮ ህሙማን መጋቢት 18/2013ዓ/ም ከቦታው ድረስ በመገኘት የበጎ ፈቃድ የአዕምሮ ህክምና እርዳታ …
በኢትዮጵያ የእንስሳት ሀኪሞች ማህበር አዘጋጅነት በአማራ ክልል በእንስሳት ህክምና ሙያ አዲስ የተመረቁ/ ስራ ፈላጊ ወጣቶች/፣ በመንግስት እንዲሁም በግል ፋርማሲ ወይም ክሊኒክ ስራ ላይ የተሰማሩ የእንስሳት ሀኪሞች መጋቢት 20/2013 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ጉብኝት አካሄዱ፡፡ የልምድ ልውውጡ Health …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን በወገራና በአርጫሆ ወረዳዎች በከብት ማድለብ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሴቶችና ወጣቶች በስራ ፈጠራ፣ በንግድ ስራ አመራር እንዲሁም በእሴት ሰንሰለት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈተቱት የኮሌጁ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ዶ/ር …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ 19 ክትባት ዛሬ ማለትም መጋቢት 20/2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሰጠት ጀመረ፡፡ በዚህ የመጀመሪያው ዙር የክትባት አሰጣጥ የተከተቡት የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ናቸው፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ በኮቪድ-19 ምክንያት ብዙ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል አዘጋጅነት “የዓባይ ውኃ ጉዳይ” በሚል መፅሐፍ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ኤፍሬም ጥሩነህ እንደገለጹት የአባይ ውኃ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳይ በመሆኑ ወርሃዊ መወያያችን በዓባይ ጉዳይ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ደን ሳይንስ ትምህርት ክፍል March 21 የሚከበረውን የአለም የደን ቀንን Forest Restoration: A path to recovery and well-being በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ አልጣሽ አዳራሽ መጋቢት 16/2013ዓ/ም በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡ በዕለቱ የኮሌጁ ዲን ተወካይ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ2013ዓ.ም እስከ 2022 ዓ.ም የሚተገብረው የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ እና የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት፣ ለአጋርና ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቅ እና ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሀ-ግብር መጋቢት 14/2013ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በመርሀ-ግብሩ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጅ እና እቅዶች ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ከመጋቢት 13-14/2013 ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን ያስጀመሩት የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ እንደገለፁት መንግስት የትምህርትን ተደራሽነት ለማስፋፋት ጥረት ቢያደረግም ከፍተኛ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ መምህራን (Improving skill and providing all office machine menetainance servies) በሚል ርዕስ ለማዕከላዊ እና ለሰሜን ጎንደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች የአይቲ ባለሙያዎች ከመጋቢት 10-11/2013ዓ/ም የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና በኮሌጁ የስልጠና ክፍል ሰጥተዋል፡፡
