የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት መጋቢት 2 እና 3 / 2013 ዓ.ም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ ግለሰቦች በጯሂት ከተማ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡ የስልጠናው አስተባባሪ እና በፋርማሲ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ እሸቴ መለሰ እንደገለፁት …
የጎርጎራ ከተማን መሪ እቅድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንዲሰራ ሃላፊነት መሰጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ የመሪ እቅድ ዝግጅቱ የደረሰበትን ደረጃ መሰረት ያደረገ ውይይት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክ ቡድን አባላትና የባህርዳር ከተማን መሪ እቅድ ባዘጋጀው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክ ቡድን መካከል ዛሬ የካቲት 27/2013 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን እንኳን ለአድዋ 125ኛ ዓመት የድል በዓል አረሳችሁ ካሉ በኋላ የአድዋ ድል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድል እንዲሁም የመላው ጥቁር ህዝብ የነፃነት ቀን በመሆኑ ልንኮራበት ይገባል ፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ከዚህ ድል አንድነትንና ፍቅርን መማር ይገባችኋል በማለት …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን በተመለከተ የባለድርሻ አካላትን አቅምና የማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ በአለፋ እና በጣቁሳ ወረዳዎች ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የካቲት 22 እና 23/2013ዓ/ም በደልጊ ከተማ የአስተዳደር የስብሰባ አዳረሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ከየወረዳዎቹ የተወጣጡ የሀገር …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና አጠ/ስ/ሆስፒታል ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት በማህበረሰቡ ውስጥ በመግባት በጤናው ዘርፍ ተግባራዊ የማህበረሰብ አገልግሎት እንደሚሰጡ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ የአካባቢና ሙያ ደህንነት /Environmental and Occupational Health / ት/ክፍል ተማሪዎች የተለያዩ በሽታዎችን ቅድመ መከላከል መሰረት ያደረገ ተግባር በተለያዩ ትምህርት …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ከጥናትና ምርምር ጽንሰ-ሀሳቦች ጋር የተያያዙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለዩኒቨርሲቲው ድህረ ምረቃ ተማሪዎች (ለ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች) ከየካቲት 17-18/2013ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት ለጎንደር ከተማ ፈለገ አብዮት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የትምህርት ቤት ነርሶች (school nurses) እና ስነ-ልቦና አማካሪዎች የአዕምሮ ጤናን በትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሳደግ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከየካቲት 10-12/2013 ተሰጠ፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት …
የአዕምሮ ጤናን በትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሳወቅ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት ለጎንደር ከተማ ፈለገ አብዮት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የትምህርት ቤት ነርሶች (school nurses) እና ስነ-ልቦና አማካሪዎች የአዕምሮ ጤናን በትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሳደግ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከየካቲት 10-12/2013 ተሰጠ፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ የውሻ ንክሻን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል በንድፈ-ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና ለእንስሳት ህክምና ሙያተኞችና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ዛሬ የካቲት 13/2013 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡ የጎንደርዩ ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሽመልስ ዳኛቸው፣ የዩኒቨርሲቲው ዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጅ …
